copticcast
copticcast 29 Feb 2020
1

Up next

Coptic Orthodox Answers (Q&A) E13: What makes Baptism so essential for my salvation?
01 Oct 2020
Coptic Orthodox Answers (Q&A) E13: What makes Baptism so essential for my salvation?
copticcast · 4 Views

ቅድስት ሙራኤል - ክፍል 1 / Kidist Murael part - 1 / Orthodox Tewahedo Film - Ye Kidusan Tarik

36 Views

ቅድስት ምህራኤል
የከበረችና የተመሰገነች ቅድስት ምህራኤል ጠምዋህ ከሚባል አገር የተገኘች ታላቅ ሰማዕት ናት፡፡ ወላጆቿ ካህኑ አባቷ ዮሐንስና እናቷ ኢላርያ እግዚአብሔርን የሚያመልኩ ደገኞች ናቸውና እርሷንም በሃይማኖት በምግባር ኮትኩተው አሳደጓት፡፡ መጀመሪያውንም ልጅ ስላልነበራቸው በስዕለት ከብዙ ዘመን በኋላ ነው ያገኟት፡፡ ስዕለታቸውም ደርሶላቸው ቅድስት ምህራኤልን ከወለዷት በኋላ ፈሪሃ እግዚአብሔርንና የቤተ ክርስቲያንን ትምህርት እያስተማሩ አሳደጓት፡፡

ቅድስት ምህራኤልም 12 ዓመት በሆናት ጊዜ በላይዋ ባደረ በመንፈስ ቅዱስ ስጦታ ድንቅ ድንቅ የሆኑ ተአምራትን መሥራት ጀመረች፡፡
ከሃዲው ንጉሥ ዲዮቅልጥያኖስ በነገሠና አምልኮተ ጣዖትን በአዋጅ ባወጀ ጊዜ ቅድስት ምህራኤል ስለ ጌታችን አምላክነት መስክራ ሰማዕት መሆንን ተመኘች፡፡ ከዚህም በኋላ በቁርጥ ሀሳብ ተነሥታ ወደ ባሕር ዳርቻ በመሄድ በመርከብ ተሳፍራ ሄዳ ስሙ ፍልፍልያኖስ የሚባለው የዲዮቅልጥያኖስ መኮንን ዘንድ ደረሰች፡፡ በመርከብም ስትጓዝ ሌሎች ስለ ቀናች እምነታቸው ሰማዕትነትን ለመቀበል የተዘጋጁ ሰማዕታትን አግኝታ ከእነርሱ ጋር ነበረች፡፡ በመኮንኑም ፊት ቆማ እውነተኛውና ሊመለክ የሚገባው አምላክ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ብቻ መሆኑን መሰከረች፡፡ መኮንኑም ስለ ታናሽነቷ ራርቶላት ከሌሎቹ ለይቶ ሊተዋት ወደደ፡፡ ነገር ግን ቅድስት ምህራኤል መኮንኑ እንደተዋት ዐውቃ የተመኘችውን ሰማዕትነት ሊያስቀርባት መሆኑን ባየች ጊዜ ዳግመኛ መኮንኑንና የረከሱ አማልክቶቹን በድፍረት ረገመችበት፡፡ ከዚህም በኋላ መኮንኑ በጣም ተቆጥቶ ጽኑ በሆኑ የተለያዩ ሥቃዮች አሠቃያት፡፡
ከቀናች ሃይማኖቷም ሸንግሎ ይመልሳት ዘንድ እንዳልተቻለው ሲያውቅ መርዛማ እባቦች፣ ጊንጦችና እፉኝቶች ወዳሉበት ጉድጓት ጣላት፡፡
ከቅድስት ምህራኤልም ጋራ ሌሎች ብዙ ሰማዕታት አብረው ተጣሉ፡፡ በዚህም ጊዜ የታዘዘ የእግዚአብሔር መልአክ ለቅድስት ምህራኤል ተገለጸላትና ከጌታችን ዘንድ የተሰጣትን ቃልኪዳን አስረከባት፡፡ ከዚህም በኋላ ነፍሷን ለእግዚአብሔር አሳልፋ ሰጥታ የሰማዕትነት አክሊልን ተቀበለች፡፡ ምእመናንም የከበረ ሥጋዋን መርዛማ እባቦችና ጊንጦች ካሉበት ቦታ አውጥተው በክብር ቀበሯት፡፡ በኋላም ወላጆቿ ልጃቸው ቅድስት ምህራኤል ስለ እምነቷ መስክራ በክብር ሰማዕት መሆኗን በሰሙ ጊዜ ከብዙ የሀገራቸው ሕዝብ ጋር መጥተው የከበረ ሥጋዋን አፍልሰው ወደ አገራቸው ወሰዱት፡፡ ያመረች ቤተ ክርስቲያንም ሠርተው ሥጋውን በውስጧ ባኖሩ ጊዜ ከሰማዕቷ ቅዱስ ሥጋ ብዙ አስገራሚ ተአምራት ተፈጽመው ታዩ፡፡ ረድኤት በረከታቷ ይደርብን በጸሎቷ ይማረን፡፡ አሜን፡፡

ከገድላት አንደበት-ke gedilat andebet የተወሰደ፡፡

Show more
0 Comments sort Sort By

Up next

Coptic Orthodox Answers (Q&A) E13: What makes Baptism so essential for my salvation?
01 Oct 2020
Coptic Orthodox Answers (Q&A) E13: What makes Baptism so essential for my salvation?
copticcast · 4 Views